በቤተ ማካና በአቤልም መጥተው ከበቡት፤ በከተማዪቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፤ እነርሱም ከአጥሩ ቀጥሎ ቆሙ፤ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ተስማሙ።
ሕዝቅኤል 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጧም የሚዋጉበት ግንብን ሥራ፤ በሠራዊትም ክበባት፤ በዙሪያዋም ጦር አስፍር፤ የሚዋጋ ጦርንም ወደ አደባባይዋ ላክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በወታደር እንደሚከበብ ክበባት፤ ምሽግ ሥራባት፤ ዐፈር ደልድልባት፤ ጦር ሰፈሮችን ቀብቅብባት፤ ቅጥር መደርመሻ ግንዶችንም በዙሪያዋ አስቀምጥባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክበባት፥ ምሽግም ሥራባት፥ ቁልልም ሥራባት፥ ሰፈርም አቁምባት፥ በዙሪያዋም ቅጥርን የሚያፈርስ ግንድ አድርግባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልክ እንደ አንድ ከተማ አስመስለህ በጡቡ ላይ አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ፤ እስከ ጫፍ ድረስ የዐፈር ቊልልና መወጣጫ ሠርተህ ጡቡን በጠላት ወታደር እንደሚከበብ አስመስለህ ክበባት። በሁሉም አቅጣጫ የእንጨት ምሰሶ ሠርተህ የከተማይቱን የቅጥር በር የምታፈርስ አስመስል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሽግም ሥራባት፥ አፈርም ደልድልባት፥ ሰፈርም አቁምባት፥ በዙሪያዋም የሚያፈርስ ግንድ አድርግባት። |
በቤተ ማካና በአቤልም መጥተው ከበቡት፤ በከተማዪቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፤ እነርሱም ከአጥሩ ቀጥሎ ቆሙ፤ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ተስማሙ።
አሕዛብም መጥተው ይህችን ሀገር ያዟት፤ ይህችም ከተማ ከረኃቡና ከጦሩ የተነሣ በወጓት በከለዳውያን ሰዎች እጅ ወደቀች፤ እንደ ተናገርኸውም ሆነ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለምሽግና ለመከላከያ ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦
ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት፤ በዙሪያዋም አራት ክንድ ግንብ ሠራ።
ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ኀይልን አፍስሱ ይህች ከተማ የሐሰት ከተማ ናት፤ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።
የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ምዋርት በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።
የእስራትህም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማዪቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጎራዴ ትመታለህ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ፤ እኔም በኋላቸው ጎራዴ እመዝዛለሁ።