ሕዝቅኤል 39:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሰበስብሃለሁ፤ እመራሃለሁ፤ ከሰሜንም ዳርቻ አወጣሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች እወስድሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ እንዲሁም እጐትትሃለሁ፤ ከሩቅ ሰሜን አምጥቼ በእስራኤል ተራሮች ላይ እሰድድሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እመልስሃለሁ፥ እመራሃለሁ፥ ከሰሜን ዳርቻ አወጣሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች እወስድሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቅጣጫውን አስለውጬ ሩቅ ከሆነው ከሰሜን አገር ገፋፍቼ በእስራኤል ተራራዎችም ላይ እንዲዘምት አደርገዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እመልስሃለሁ፥ እነዳህማለሁ፥ ከሰሜንም ዳርቻ እጐትትሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች አመጣሃለሁ። |
የተቈጣኸው ቍጣና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ሰለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።
ከአልተገረዙና ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል፤ የሰሜን አለቆች ሁሉ፥ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኀይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሀት አፍረዋል፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ያልተገረዙት ተኝተዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ቅጣታቸውን ተሸክመዋል።
አንተም፥ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላቸው በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ታላቅ ወገንና ብርቱ ሠራዊት፥ ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሮስ የሞሣሕና የቶቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤
ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፤ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ እጥልሃለሁ።