La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 38:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እንደ ዝናም ትወ​ጣ​ለህ፤ እንደ ደመ​ናም ምድ​ርን ትሸ​ፍን ዘንድ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ አን​ተም ከብዙ ሕዝ​ብና ሠራ​ዊት ጋር ትወ​ድ​ቃ​ለህ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንተና ወታደሮችህ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ ያሉት ብዙ ሕዝቦች እንደ ማዕበል ትወጣላችሁ፤ ምድርን እንደሚሸፍን ደመናም ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተም ወደ ላይ ትወጣለህ፥ እንደ ማዕበል ትመጣለህ፤ አንተና ሠራዊትህ ሁሉ፥ ብዙ ሕዝብም ከአንተ ጋር ሆነው ምድርን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱና ሠራዊቱ፥ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ያሉ ብዙ ሕዝብ እንደ ማዕበል ሞገድ ሆነው ይመጣሉ፤ እንደ ደመናም ሆነው ምድሪቱን ይሸፍናሉ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ፥ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድርን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 38:9
12 Referencias Cruzadas  

ለተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ከተ​ሞች ረዳት ሆነ​ሃ​ልና፥ በች​ግ​ራ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁ​ትን በደ​ስታ ጋረ​ድ​ሃ​ቸው፤ ከክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም አዳ​ን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ጠ​ሙት ጥላ ሆን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ገ​ፉ​ትም ሕይ​ወት ሆን​ሃ​ቸው።


እነሆ፥ ኀያል ብርቱ የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ የበ​ረዶ ወጨፎ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋም ዐውሎ ነፋስ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ በጠ​ነ​ከረ እጅ ወደ ምድር ይጥ​ላል።


ፍላ​ጾ​ቻ​ቸው ተስ​ለ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተለ​ጥ​ጠ​ዋል፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም መን​ኰ​ራ​ኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈ​ጠ​ራል።


እነሆ! እንደ ደመና ይወ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረ​ሶ​ቹም ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ናቸው። ተዋ​ር​ደ​ና​ልና ወዮ​ልን።


ያለ ገለ​ባም ለሚ​መ​ር​ጉት ሰዎች፦ ይወ​ድ​ቃል በላ​ቸው። የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ ይዘ​ን​ባል፤ ታላ​ቅም የበ​ረዶ ድን​ጋይ በራ​ሳ​ቸው ላይ አወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ኀይ​ለኛ ዐውሎ ነፋ​ስም ይሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋል።


የግ​ብ​ፅን ቀን​በር በዚያ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ በጣ​ፍ​ናስ ቀኑ ይጨ​ል​ማል፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ትዕ​ቢት ይጠ​ፋ​ባ​ታል፤ ደመ​ናም ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ዋም ይማ​ረ​ካሉ።


ምድ​ር​ንም ትሸ​ፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትወ​ጣ​ለህ። በኋ​ለ​ኛው ዘመን ይሆ​ናል፤ ጎግ ሆይ! በፊ​ታ​ቸው በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ብህ ጊዜ፥ አሕ​ዛብ ያው​ቁኝ ዘንድ በም​ድሬ ላይ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ።


የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።


ወደ ምድርም ስፋት ወጡ፤ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው።