ሕዝቅኤል 32:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማታውቃቸውም ሀገሮች በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ድል መሆንህን በአሰማሁ ጊዜ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማታውቀው ምድር፣ በሕዝቦች መካከል ያንተን ጥፋት ሳመጣ፣ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማታውቃቸውም አገሮች ባሉ በአሕዛብ ዘንድ ስብራትህን ባመጣሁ ጊዜ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በማታውቃቸው ሕዝቦች መካከል የጥፋትህን ዜና በማሰማበት ጊዜ የብዙ ሕዝቦችን ልብ አስጨንቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማታውቃቸውም አገሮች ባሉ በአሕዛብ ዘንድ ጥፋትህን ባመጣሁ ጊዜ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ። |
ቀዛፊዎችም ሁሉ፥ በመርከብ የተጫኑትም መርከብ መሪዎችም ሁሉ ከመርከቦቻቸው ይወርዳሉ፤ በየብስም ላይ ይቆማሉ፤
ባድማም በሆኑ ምድሮች መካከል የግብፅን ምድር ባድማ አደርጋታለሁ፤ በፈረሱትም ከተሞች መካከል ከተሞችዋ አርባ ዓመት ፈርሰው ይቀመጣሉ፤ ግብፃውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናቸዋለሁ፤ በሀገሮችም እዘራቸዋለሁ።”
ግብፃውያንንም በአሕዛብ መካከል እበትናለሁ፤ በሀገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ በግብፅም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ፥ ይመጣልና።
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”