ሕዝቅኤል 32:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰፊ ምድረ በዳም እጥልሃለሁ፤ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፤ የምድርንም አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድር ላይ እጥልሃለሁ፤ ሜዳም ላይ እዘረጋሃለሁ፤ የሰማይ ወፎች ሁሉ እንዲሰፍሩብህ አደርጋለሁ፤ የምድር አራዊት ሁሉ በመስገብገብ ይበሉሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ እተውሃለሁ፥ ለጥ ባለ ሜዳም እጥልሃለሁ፥ የሰማይ ወፎች ሁሉ በአንተ ላይ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፥ የምድርን አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትቢያም ላይ እጥልሃለሁ፤ ሥጋህንም እንዲመገቡት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊትን ሁሉ እጠራለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም ላይ እተውሃለሁ፥ በምድረ በዳም ፊት እጥልሃለሁ፥ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፥ የምድርንም አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ። |
ለሰማይ ወፎችና ለምድር አውሬዎችም በአንድነት ይቀራሉ፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አውሬዎችም ሁሉ ይሰበሰቡባቸዋል።
ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸውም አይጠፋም፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆናሉ።”
በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም፤ አይቀበሩምም።
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
አንተንና የወንዞችህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ፤ በምድርም ፊት ላይ ትወድቃለህ እንጂ አትከማችም፤ አትሰበሰብምም፤ መብልም አድርጌ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች ሰጥቼሃለሁ።
ተራሮችህንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኮረብቶችህና በሸለቆዎችህ፥ በፈሳሾችህም ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ ይወድቃሉ።
በሀገራቸው ንጹሑን ደም አፍስሰዋልና በይሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደረጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶምያስም በረሃ ይሆናል።