በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን ፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና የመሣሪያዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።
ሕዝቅኤል 26:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግንቦችሽንና ቅጥርሽን በምሳር ያፈርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግንብ መደርመሻውን በቅጥሮቿ ላይ ያነጣጥራል፤ በመሣሪያም ምሽጎችሽን ያፈርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግንብ ማፍረሻውን በቅጥርሽ ላይ ያነጣጥራል፥ ግንብሽንም በሰይፉ ያፈርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምሽግ ማፍረሻ መሣሪያ ቅጽሮችሽን ይመታል፤ የዘብ መጠበቂያ ግንብሽን በምሳር ያፈራርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማፍረሻውን በቅጥርሽ ላይ ያደርጋል፥ ግንቦችሽንም በምሳር ያፈርሳል። |
በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን ፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና የመሣሪያዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።
የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ምዋርት በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።
ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ በትቢያ ይሸፍንሻል፤ ከሠረገላ መንኰራኵርና ከፈረሶቹ ድምፅ የተነሣም ቅጥሮችሽን ያፈርሳል፤ ወንበዴ መሣሪያውን ይዞ ወደ ምድረ በዳ ቦታ እንዲገባ በሮችሽን ይገቡባቸዋል።
የጢሮስንም ቅጥሮች ያፈርሳሉ፤ ግንቦችዋንም ያፈርሳሉ፤ ትቢያዋንም ከእርስዋ እፍቃለሁ፤ እንደ ተራቈተ ድንጋይም አደርጋታለሁ።
እርሱ በምድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ ጠባቂዎችንም በአንቺ ላይ ያስቀምጣል፤ በዙሪያሽም ግንብ ይሠራል፤ የጦር መሣሪያም ይዘው ይከቡሻል፤ በጦራቸውም ይወጉሻል፤