ነገሥታቱን ያበሳጨቻቸው የባሕር ሰዎች እጃቸው ትደክማለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የከነዓንን ኀይል ያጠፉ ዘንድ አዘዘ።
ሕዝቅኤል 26:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጢሮስንም ቅጥሮች ያፈርሳሉ፤ ግንቦችዋንም ያፈርሳሉ፤ ትቢያዋንም ከእርስዋ እፍቃለሁ፤ እንደ ተራቈተ ድንጋይም አደርጋታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጢሮስን ቅጥሮች ያወድማሉ፤ ምሽጎቿንም ያፈርሳሉ። ዐፈሯን ከላይዋ ጠርጌ የተራቈተ ዐለት አደርጋታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጢሮስን ቅጥሮች ያፈርሳሉ፥ ግንቦችዋንም ያፈርሳሉ፤ አፈሯን ከእርሷ ላይ ጠርጌ የተራቆተ ዓለት አደርጋታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተማሽን የቅጽር ግንቦች ያፈራርሳሉ፤ የዘብ መጠበቂያ ግንብሽን ይሰባብራሉ፤ ዐፈሩን ሁሉ ጠራርጌ በማጥፋት አለቱ ብቻ አግጥጦ እንዲቀር አደርጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጢሮስንም ቅጥሮች ያጠፋሉ ግንቦችዋንም ያፈርሳሉ፥ ትቢያዋንም ከእርስዋ እፍቃለሁ፥ የተራቈተ ድንጋይ አደርጋታለሁ። |
ነገሥታቱን ያበሳጨቻቸው የባሕር ሰዎች እጃቸው ትደክማለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የከነዓንን ኀይል ያጠፉ ዘንድ አዘዘ።
“ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፤ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የእግዚአብሔር ናቸውና መጠጊያዎችዋን አትርፉ።
ገንዘብሽን ይበረብራሉ፤ መንጋሽንም ይዘርፋሉ፤ አምባሽንም ይንዳሉ፤ የተወደዱ ቤቶችሽንም ያፈርሳሉ፤ እንጨቶችሽንና ድንጋይሽን፥ መሬትሽንም በባሕሩ ጥልቅ ውስጥ ይጥሉታል።