ሕዝቅኤል 26:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ ባሕርም ሞገድዋን እንደምታወጣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን አወጣብሻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ጢሮስ ሆይ፤ እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ባሕር ሞገዷን እንደምታስነሣ፣ ብዙ ሕዝብ አስነሣብሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፥ ባሕር ሞገድን እንደሚያስነሣ እንዲሁ ብዙ ሕዝቦችን አስነሣብሻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ! እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼ ባሕር ሞገድን እንደሚያስነሣ በአንቺ ላይ ብዙ ሕዝቦቼን አስነሣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ባሕርም ሞገድዋን እንደምታወጣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን አወጣብሻለሁ። |
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
ትዕቢተኛ ሆይ! አንቺን የሚበቀሉበት ጊዜ፥ ቀንሽ ደርሶአልና እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ቀስትና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፤ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።
ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ በሰረገላና በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠፉሻል።
ለእስራኤልም ምድር እንዲህ በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ ሰይፌንም ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፤ ጻድቁንና ኃጥኡን ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰው እንደሌለባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ቀላዩንም ባወጣሁብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆችም በከደኑሽ ጊዜ፥
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ በውስጥሽም እከብራለሁ፤ ፍርድንም በአደረግሁብሽ ጊዜ፥ በተቀደስሁብሽም ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
ስለዚህ፥ እነሆ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ በጦርና በቸነፈር ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሮስ፥ የሞሣሕና የቶቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፤ በአሕዛብም ፊት ፍርድን በመካከልሽ አደርጋለሁ።
እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ እገልጣለሁ፣ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።
አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፣ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፣ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።
“በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ይጨነቃሉ፤ ከባሕሩና ከሞገዱ ድምፅ የተነሣም ይሸበራሉ።