እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ለጥፋትና ለተረት ይሆናሉ።
ሕዝቅኤል 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባፈሰስሽው ደም በድለሻል፤ ባደረግሻቸውም ጣዖታት ረክሰሻል፤ ቀንሽንም አቀረብሽ፤ ዘመንሽንም አሳጠርሽ፤ ስለዚህ ለአሕዛብ መሰደቢያ፥ ለሀገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደረግሁሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባፈሰስሽው ደም በድለሻል፤ በሠራሽውም ጣዖት ረክሰሻል፤ ከዚህም የተነሣ ቀንሽን አቅርበሻል፤ ዕድሜሽንም አሳጥረሻል። ስለዚህ ለአሕዛብ መዘባበቻ፣ ለአገሩም ሁሉ መሣለቂያ አደርግሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባፈሰስሽው ደም በድለሻል፥ በሠራሻቸውም ጣዖቶችሽ ረክሰሻል፥ ቀንሽን አቀረብሽ፥ ዘመንሽንም አሳጠርሽ፥ ስለዚህ ለሕዝቦች መሰደቢያ፥ ለአገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደረግሁሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፈጸምሽው ግድያ በደለኛ ሆነሻል፤ በሠራሻቸውም ጣዖቶች ረክሰሻል፤ ስለዚህ የምትጠፊበት ጊዜ ቀርቦአል! ያፋጠንሽውም አንቺ ነሽ። ሕዝቦች እንዲቀልዱብሽ፥ አገሮችም በንቀት አመለካከት እንዲያፌዙብሽ ያደረግኹትም ስለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባፈሰስሽው ደም በድለሻል ባደረግሽውም ጣዖታት ረክሰሻል፥ ቀንሽን አቀረብሽ ዘመንሽንም አሳጠርሽ፥ ስለዚህ ለአሕዛብ መሰደቢያ ለአገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደረግሁሽ። |
እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ለጥፋትና ለተረት ይሆናሉ።
ደግሞም ምናሴ በእግዚአብሔር ዐይኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁዳን ካሳተበት ኀጢአት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየሩሳሌምን እስኪሞላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈሰሰ።
እኔም ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላችኋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ በአሕዛብም ሁሉ መካከል ምሳሌና ተረት አደርገዋለሁ።
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፥ ለጥላቻና ለርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲበተኑ አደርጋለሁ።
ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፥ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
ክፋትሽ እንደ ዛሬው ሳይገለጥ ለሶርያ ሴቶች ልጆችና ለጐረቤቶችዋ ሁሉ በዙሪያሽም ለሚከቡሽ ፍልስጥኤማውያት ሴቶች ልጆች መሰደቢያ ሆነሻል።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመግደል ተመዝዞአል፤ ጨርሶም ያርድ ዘንድ ተሰንግሎአል በል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የጠለቀውንና የሰፋውን፥ ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙ መጠጥን በሚጠጡ ሰዎችም ዘንድ መሳቂያና መሳለቂያ ትሆኛለሽ።
ደምዋም በመካከልዋ አለ። በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።
ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አትሸከሚም፤ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
እነሆም፥ የእግዚአብሔርን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ትጨምሩ ዘንድ እናንተ በኀጢአተኞች ሰዎች በደል በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሥታችኋል።
አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ስለ ምን እንደዚህ አደረገ? ይህስ የቍጣው ታላቅ መቅሠፍት ምንድን ነው? ይላሉ።