ሕዝቅኤል 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ፥ እንድትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በመካከልሽ ደምን በማፍሰስና ጣዖታትን በመሥራት ራስሽን የምታረክሺ፣ ፍርድንም በራስሽ ላይ የምታፈጥኚ ከተማ ሆይ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ ከተማ ሆይ!ጊዜዋ ደርሶአል፥ እንድትረክስም በራስዋ ላይ ጣዖታትን የምታደርግ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለከተማይቱ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ በውስጥሽ ያሉትን ብዙዎችን ስለ ገደልሽና ጣዖቶችን በማምለክ ራስሽን ስላረከስሽ እንድትጠፊ የተወሰነበት ጊዜ ተቃርቦአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ እንዲትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ! |
ፍርድ መልቶባት የነበረ የታመነችይቱ የጽዮን ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፤ አሁን ግን ወንበዴዎችና ነፍሰ ገዳዮች አሉባት።
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ይፈጸማል፤ ደግሞም አይዘገይም፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ! በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ፤ እፈጽመውማለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
ባፈሰስሽው ደም በድለሻል፤ ባደረግሻቸውም ጣዖታት ረክሰሻል፤ ቀንሽንም አቀረብሽ፤ ዘመንሽንም አሳጠርሽ፤ ስለዚህ ለአሕዛብ መሰደቢያ፥ ለሀገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደረግሁሽ።
አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፥ ዝሙታቸውንም ወድደዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን መብል እንዲሆኑላቸው በእሳት አሳልፈዋቸዋልና።
ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በእጃቸውም ደም አለና ጻድቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል።”
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፤ ዐይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
እርሱም፥ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኀጢአት እጅግ በዝቶአል፤ ምድሪቱም በብዙ አሕዛብ እንደ ተመላች ከተማዪቱም እንዲሁ ዓመፅንና ርኵሰትን ተሞልታለች፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል፤ እግዚአብሔርም አያይም” ብለዋል።
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።