የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፥ “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ” ብሎ ነገረው። ኤልያስም ተነሥቶ ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።
ሕዝቅኤል 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ እነርሱን ወይም ቃላቸውን አትፍራ፤ ኵርንችትና እሾኽ በዙሪያህ ቢኖሩም፣ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም አትፍራ። እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ቢሆኑም፣ አንተ በሚሉህ ነገር አትፍራ፤ እነርሱም አያስደንግጡህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራ፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቃላቸውን አትፍራ፥ ፊታቸውንም አትፍራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን የሰው ልጅ ሆይ! እነርሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ፤ እንደ እሾኽና እንደ አሜከላ ሆነውብህ በጊንጦች መካከል እንደምትኖር ሆነህ ቢሰማህም ቃላቸውንም ሆነ የእነዚያን ዐመፀኞች የቊጣ ፊት ከቶ አትፍራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ኵርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራቸው፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና። |
የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፥ “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ” ብሎ ነገረው። ኤልያስም ተነሥቶ ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።
እኔ ነኝ፤ የማጽናናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እንግዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ነውን?
ኀጢአት እንደ እሳት ይነድዳል፤ እሳት እንደ በላችው ደረቅ ሣር ይቃጠላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃጠላል፤ በተራራዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃጠላል።
አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥም፤ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ። በፊታቸውም አትደንግጥ አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ይላል እግዚአብሔር።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
ለዐመፀኛውም ቤት ምሳሌን ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ድስቲቱን ጣድ፥ ውኃም ጨምርባት።
ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ከአሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቈስል ኩርንችት አይሆንም፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።
እነሆ፥ ጊንጦችንና እባቦችን፥ የጠላትንም ኀይል ሁሉ ትረግጡ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ፤ የሚጐዳችሁም ነገር የለም።
ለእናንተ ለወዳጆች እላችኋለሁ፦ ሥጋችሁን የሚገድሉትን አትፍሩአቸው፤ ከዚህም የበለጠ ማድረግ የሚችሉት የላቸውም።
ጴጥሮስና ዮሐንስም ግልጥ አድርገው ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፥ ያልተማሩና መጽሐፍን የማያውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐውቀው አደነቁ፤ ሁልጊዜም ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።
ጴጥሮስና ዮሐንስም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፥ “እግዚአብሔርን ያይደለ እናንተን ልንሰማ በእግዚአብሔር ፊት ይገባልን? እስኪ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።