ሕዝቅኤል 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴም ዘረጋው፤ በውስጥና በውጭም ተጽፎበት ነበረ፤ ጽሑፉም “ልቅሶና ኀዘን፥ ዋይታም” ይል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በፊቴ ዘረጋው፤ መጽሐፉም ከፊትና ከኋላው የሰቈቃ፣ የልቅሶና የዋይታ ቃላት ተጽፎበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቴም ዘረጋው፥ በፊቱና በኋለውም ልቅሶ፥ ኃዘንና ዋይታም ተጽፎበት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም እጅ የብራናውን ጥቅል ፈቶ በፊቴ ዘረጋው፤ እርሱም በሁለት በኩል ጽሑፍ ያለበት መሆኑን አየሁ፤ በእርሱም ላይ የለቅሶ፥ የሐዘንና የዋይታ ቃሎች ተጽፈውበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊቴም ዘረጋው፥ በውስጥና በውጭም ተጽፎበት ነበር፥ ልቅሶና ኃዘን ዋይታም ተጽፎበት ነበር። |
አየሁም፤ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ “ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” ሲል ሰማሁ።