የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
ሕዝቅኤል 17:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀንበጡንም ቀነጠበ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ወሰደው፤ ቅጥር ባለው ከተማም አኖረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጫፉም የላይኛውን ቀንበጥ ቀንጥቦ ወደ ነጋዴዎች ምድር ወሰደ፤ በሸቀጥ ነጋዴዎችም ከተማ ተከለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀንበጡንም ቀነፈ፥ ወደ ከነዓንም ምድር አመጣው፥ በነጋዴዎችም ከተማ ተከለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀንበጡንም ቀነጠበ ወደ ከነዓንም ምድር ወሰደው በነጋዶችም ከተማ አኖረው። |
የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፤ ስደተኞችን አስነሣለሁ፤ ከለዳውያንም በመርከብ ውስጥ ይታሰራሉ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ፥ ረጅምም ጽፍር ያለው፥ ላባንም የተሞላ፥ መልከ ዝንጉርጉር የሆነ ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፤ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።
እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍግነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመናዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ነበረ።
አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።