ሕዝቅኤል 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ! ዐመፀኛ ቤት የእስራኤል ቤት፦ የምታደርገው ምንድር ነው? አላሉህምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ ዐመፀኛው የእስራኤል ቤት፣ ‘ይህ የምታደርገው ምንድን ነው?’ ብለው ጠይቀውህ አልነበረምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት፥ ዓመፀኛ ቤት፦ ምን እያደረግህ ነው? አላሉህምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚያ ዐመፀኞች እስራኤላውያን ‘እነሆ ይህ የምታደርገው ነገር ሁሉ ምንድን ነው?’ ብለው አልጠየቁህምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓመፀኛ ቤት የእስራኤል ቤት፦ የምታደርገው ምንድር ነው? አላሉህምን? አንተም፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአስቈጡኝ ለእስራኤል ቤት ይህ ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? በላቸው። እንዲህም ብለህ ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፤ ወደ ሀገሩም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።
የሕዝብህም ልጆች፦ ይህ የምታደርገው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ አትነግረንምን? ብለው በተናገሩህ ጊዜ፥ አንተ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦