በእንስሶቹም መካከል እንደሚነድድ የእሳት ፍም ያለ አምሳያ ነበረ፤ በእንስሶቹ መካከል ወዲህና ወዲያ የሚሄድ እንደ ፋና ያለ አምሳያ ነበረ፤ ለእሳቱም ፀዳል ነበረው፤ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።
ሕዝቅኤል 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኪሩቤል መካከልም አንዱ ኪሩብ እጁን በኪሩቤል መካከል ወደ አለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ እሳት ወሰደ፤ የተቀደሰ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው፤ እርሱም ይዞ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ወዳለው እሳት እጁን ዘርግቶ ጥቂት ወሰደ፤ በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ እርሱም ይዞ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኪሩቤል መካከል አንድ ኪሩብ እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታ በለበሰው ሰው እጅም አኖረው፥ እርሱም ይዞ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ባለው እሳት ውስጥ እጁን ሰድዶ ጥቂት ፍሞች አነሣና በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ ሰውየውም ፍሙን ይዞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኪሩብም ከኪሩቤል መካከል እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው፥ እርሱም ይዞ ወጣ። |
በእንስሶቹም መካከል እንደሚነድድ የእሳት ፍም ያለ አምሳያ ነበረ፤ በእንስሶቹ መካከል ወዲህና ወዲያ የሚሄድ እንደ ፋና ያለ አምሳያ ነበረ፤ ለእሳቱም ፀዳል ነበረው፤ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።
የተቀደሰ በፍታም የለበሰውን ሰው፥ “ከመንኰራኵሮቹ ከኪሩቤል መካከል እሳት ውሰድ” ብሎ በአዘዘው ጊዜ እርሱ ገብቶ በመንኰራኵር አጠገብ ቆመ።