የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
ሕዝቅኤል 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍታም የለበሰውን ሰው፥ “በመንኰራኵሮች መካከል በኪሩብ በታች ግባ፤ ከኪሩቤልም መካከል ከአለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “በኪሩቤል ሥር ወዳሉት መንኰራኵሮች መካከል ግባ፤ በኪሩቤል መካከል ካለውም የእሳት ፍም እጅህን ሞልተህ ዝገን፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” አለው። ሰውየውም እያየሁት ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍታም የለበሰውን ሰው እንዲህ አለው፦ በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትናት ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ቀጭን ሐር የለበሰውን ሰው “ከሕያዋን ፍጥረቶች በታች ባሉት መንኰራኲሮች መካከል አልፈህ ሂድ፤ ከከሰልም ፍም በእጅህ አፍሰህ ውሰድና በከተማይቱ ላይ በትነው!” አለው። እኔም እያየሁት ገባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍታም የለበሰውን ሰው፦ በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትናት ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ። |
የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
እግዚአብሔርም የድምፁን ክብር ያሰማል፤ የክንዱንም መፈራት፥ በጽኑ ቍጣና በምትበላ እሳት፥ በወጀብም፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በበረዶም ድንጋይ ይገልጣል።
በእንስሶቹም መካከል እንደሚነድድ የእሳት ፍም ያለ አምሳያ ነበረ፤ በእንስሶቹ መካከል ወዲህና ወዲያ የሚሄድ እንደ ፋና ያለ አምሳያ ነበረ፤ ለእሳቱም ፀዳል ነበረው፤ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።
ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ ከእነርሱ ጋር ተያይዘው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩቤልም ይበሩ ዘንድ ክንፋቸውን ከምድር በሚያነሡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የተያያዘ መንኰራኵራቸው አይመለስም ነበር።
እነሆም በፍታ የለበሰው፥ የሰንፔር መታጠቂያም በወገቡ የታጠቀው ሰው መጣ፥ “ያዘዝኸኝንም አድርጌአለሁ” ብሎ በቃሉ መለሰ።