ሕዝቅኤል 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሁሉም ክንፎቻቸው አንዱ ከአንዱ ጋር የተያያዘ ነው፤ ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ ሳይሉ አቅንተው ይሄዳሉ፤ አንዱም አንዱም ወደፊቱ ይሄዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክንፎቻቸውም እርስ በርስ ይነካኩ ነበር። እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር፤ ወደ ኋላቸውም ዞር ብለው አይመለከቱም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ ይነካካ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም፥ እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእያንዳንዱ ፍጥረት ሁለት ክንፎች ግራና ቀኝ ተዘርግተው ጫፎቻቸው ይነካካሉ፤ ስለዚህ ሰውነታቸው ወዲያና ወዲህ ሳይል በኅብረት ይንቀሳቀሱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ የተያያዘ ነበረ፥ ሲሄዱም አይገላምጡም ነበረ፥ እያንዳንዱም ፊቱን አቅንቶ ይሄድ ነበር። |
ሲሔዱም በአራቱ ጎድናቸው ይሄዱ ነበር። ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር፤ መጀመሪያው ወደሚያመለክትበት ስፍራ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር።
ፊቶቻቸውም በኮቦር ወንዝ ከእስራኤል አምላክ ክብር በታች ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፤ እነርሱና መልካቸውም እንዲሁ ነበረ፤ እያንዳንዱም አቅንቶ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማንም ዕርፍ ይዞ እያረሰ ወደ ኋላው የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይሆንም” አለው።
ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ።