ሕዝቅኤል 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክንፎቻቸውም በታች በእየአራቱ ጐድናቸው የሰው እጅ ነበረ፤ ለአራቱም እንደዚህ ያሉ ፊትና ክንፍ ነበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራቱ ጐኖቻቸው ባሉት ክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ ነበራቸው። አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከክንፎቻቸውም ስር በአራቱም ጎናቸው የሰው እጆች ነበሩ፤ አራቱም ፊቶቻቸውና ክንፎቻቸው እንዲህ ነበሩ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአራቱ ፊቶቻቸውና ከአራቱ ክንፎቻቸው ሌላ እያንዳንዳቸው ከክንፎቻቸው ግርጌ አራት የሰው ዐይነት እጆች ነበሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክንፎቻቸውም በታች በእያራቱ ጐድናቸው እንደ ሰው እጅ ነበረ፥ ለአራቱም እንደዚህ ያሉ ፊትና ክንፍ ነበሩአቸው። |
ሲሔዱም በአራቱ ጎድናቸው ይሄዱ ነበር። ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር፤ መጀመሪያው ወደሚያመለክትበት ስፍራ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር።
በፍታም የለበሰውን ሰው፥ “በመንኰራኵሮች መካከል በኪሩብ በታች ግባ፤ ከኪሩቤልም መካከል ከአለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ።
ለእያንዳንዱ አራት አራት ፊት፥ ለእያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት፤ የሰውም እጅ አምሳያ ከክንፎቻቸው በታች ነበረ።
እጅ መሳይንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ ቅንአት የተባለው ምስል ወደ አለበት አመጣኝ፤