ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፤ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፤ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይሁን።
ሕዝቅኤል 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእያንዳንዱም አራት አራት ፊት፥ ለእያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዳቸውም አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዳቸውም አራት ፊቶች፥ እያንዳንዳቸውም አራት ክንፎች ነበራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱም ፍጥረት አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእያዳንዱም አራት አራት ፊት፥ ለእያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት። |
ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፤ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፤ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይሁን።
ሱራፌልም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለቱ ክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው እግሮቻቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው ይበርሩ ነበር።
ከጠፈሩም በታች ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተቃንተው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ገላውን የሚከድኑ ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሩት።
ለእያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፤ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛውም የሰው ፊት፥ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም የንስር ፊት ነበረ።