ዘፀአት 39:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳኑንም፥ መደረቢያውንም፥ ዕቃውንም ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡ፤ መያዣዎቹን፥ ሳንቆቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹንም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የማደሪያውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡት፦ እነዚህም ድንኳንና ዕቃዎቹ ሁሉ፣ ማያያዣዎችን፣ ክፈፎችን፣ አግዳሚዎችን፣ ቋሚዎችንና መሠረቶችን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማደሪያውን ወደ ሙሴ አመጡት፥ ድንኳኑን፥ የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቆቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶቹንና እግሮቹን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ዕቃዎች ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡአቸው፤ ድንኳኑንና የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ እነርሱም፦ ኩላቦቹ፥ ተራዳዎቹ መወርወሪያዎቹ፥ ምሰሶዎቹና የሚቆሙባቸው እግሮች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማደሪያውንም፥ ድንኳኑንም፥ ዕቃውንም ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡ፤ መያዣዎቹን፥ ሳንቆቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም፤ |
እንዲሁም የምስክሩ ድንኳን ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ የእስራኤል ልጆች አደረጉ፤ እንዲሁ አደረጉ።