ዘፀአት 36:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማይነቅዝም ዕንጨት አራት ምሰሶዎች አደረጉለት፤በወርቅም ለበጡአቸው፤ ኵላቦቻቸውም የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለርሱም አራት ምሰሶዎች ከግራር ዕንጨት ሠርተው በወርቅ ለበጧቸው፤ ለእነርሱም አራት የወርቅ ኵላቦችንና አራት የብር መቆሚያዎችን አበጁላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አራት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኩላቦቻቸው የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች ሠራላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጋረጃዎቹን የሚያያይዙ አራት ምሰሶዎችንም ከግራር እንጨት ሠርተው በወርቅ ለበጡአቸው፤ ኩላቦቻቸውንም ከወርቅ ሠሩ፤ ምሰሶዎቹ የሚቆሙባቸውን አራት እግሮችንም ከብር ሠሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግራርም እንጨት አራት ምሰሶች አደረጉለት፥ በወርቅም ለበጡአቸው፤ ኩላቦቻቸው የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች አደረጉ። |
“መጋረጃውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም አድርግ፤ በሽመና ሥራም ኪሩቤልን ሥራ።
መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ፤ ኪሩቤልንም በጥልፍ ሥራ በእርሱ ላይ አደረጉ።
ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አደረጉ፤
እነሆ በምድሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናቷ ላይ፥ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።