ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ይሁኑለት፤ ለድንኳኑ ሳንቆች ሁሉ እንዲሁ አድርግ።
ዘፀአት 36:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሃያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮች አደረጉ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእያንዳንዱ ጕጠት አንድ መቆሚያ፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያ ሆኖ አርባ የብር መቆሚያዎችን አበጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሃያው ሳንቃዎች በታች አርባ የብር እግሮችን አደረገ፤ በአንደኛው ሳንቃ ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች፥ በሁለተኛው ሳንቃ ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኻያውም ተራዳዎች በታች ሁለት ማገጣጠሚያ ጒጦች ባሉት በእያንዳንዱ ተራዳ ሥር ሁለት ሁለት በማኖር አርባ የብር እግሮችን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሀያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮች አደረጉ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ነበሩ። |
ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ይሁኑለት፤ ለድንኳኑ ሳንቆች ሁሉ እንዲሁ አድርግ።
ከሃያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ። ከሌላውም ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ።