ዘፀአት 36:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዱም መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያንዳንዱም መጋረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የእያንዳንዱም መጋረጃ መጠኑ ትክክል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥራ አንዱ መጋረጃዎች ተመሳሳይ ልክ ሲኖራቸው፣ ቁመታቸው ሠላሳ ክንድ፣ ወርዳቸውም አራት ክንድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሠላሳ ክንድ፥ የእያንዳንዱም መጋረጃ ወርድ አራት ክንድ ነበረ፤ የዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች መጠን እኩል ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሁሉም መጠን እኩል ሆኖ የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ዐሥራ ሦስት ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሁለት ሜትር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያንዳንዱም መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያንዳንዱም መጋረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የአሥራ አንዱም መጋረጆች መጠናቸው ትክክል ነበረ። |
አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ አደረጉ፤ ስድስቱንም መጋረጃዎች አንድ አድርገው አጋጠሙአቸው።