ዘፀአት 35:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያዊም፥ ሐምራዊም፥ ድርብ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግ፤ ቀጭን ሐር፣ የፍየል ጠጕር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥሩ ከፈይ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ቀለም የተነከረ የበግ ጠጒር፥ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰማያዊም ሐምራዊም ቀይ ግምጃም፥ ጥሩ በፍታም፥ የፍየል ጠጉርም፤ |
“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።
“መጋረጃውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም አድርግ፤ በሽመና ሥራም ኪሩቤልን ሥራ።
ለድንኳኑ ደጃፍም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ ከጥሩ በፍምታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አድርግለት።
“ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ የፍርዱን ልብሰ እንግድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መትከፍም አሠራር ሥራው፤ ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍታም ሥራው።
በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ ሮማኖችን አድርግ፤ በእነዚያም መካከል በዙሪያው በተመሳሳይ ቅርጽ የወርቅ ሮማኖች ሻኵራዎችን አድርግ፤
ከእናንተ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቍርባንን አቅርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው ከገንዘቡ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር ያምጣ፤ ወርቅና ብር፥ ናስም፤