ዘፀአት 35:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፥ “እዩ፥ እግዚአብሔር ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን አላቸው፤ “እነሆ፤ እግዚአብሔር ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሑር ልጅ፣ የኡሪን ልጅ ባስልኤልን መርጧል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ተመልከቱ፥ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሑር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ለእስራኤላውያን እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ከይሁዳ ወገን የሑር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪ ልጅ ባጽልኤልን መርጦታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፦ እዩ፥ እግዚአብሔር ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው። |
እግዚአብሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠራቢዎች አለቃ ሆኜ እኔ መሠረት ጣልሁ፤ ሌላውም በእርሱ ላይ ያንጻል፤ እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።