በየዓመቱም የመሬታችንን እህል ቀዳምያት፥ የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ቀዳምያት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
ዘፀአት 34:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወስዳለህ። ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የምድርህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቤት አምጣ። “ጠቦት ፍየልን በእናቱ ወተት አትቀቅል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ ጌታ አምላክህ ቤት ታስገባለህ። ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በየዓመቱ የመከራችሁን በኲራት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግም ሆነ የፍየል ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅልም። |
በየዓመቱም የመሬታችንን እህል ቀዳምያት፥ የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ቀዳምያት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት የአምላካችሁን ቍርባን እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዐት ነው።
መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ አንድ እንጎቻ ለይታችሁ ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደምትለዩት ቍርባን እንዲሁ ትለያላችሁ።
ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡት በምድራቸው ያለው የፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው፤
የበከተዉን ሁሉ አትብሉ፤ ይበላው ዘንድ በሀገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ወይም ለባዕድ ስጠው፤ አንተ ለአምላካህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።
አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ፍሬ ሁሉ ቀዳምያት ውሰድ፤ በዕንቅብም አድርገው፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደ መረጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።