በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
ዘፀአት 34:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብን ከፊትህ በአወጣሁ ጊዜ ሀገርህን አሰፋለሁ፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊትም ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብን ከፊትህ አስወጣለሁ፤ ድንበርህን አሰፋለሁ፤ በዓመት ሦስት ጊዜ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ማንም አይመኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብን ከፊትህ አስወግዳለሁ፥ ድንበርህንም አሰፋለሁ፤ በጌታ አምላክህ ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሕዛብን ሁሉ አስወግጄ ግዛታችሁን አሰፋለሁ፤ ስለዚህ በእነዚህ በሦስት በዓላት ወቅት ወደ እኔ ስትቀርቡ አገራችሁን ለመውረር የሚመኝ ማንም አይመጣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብን ከፊትህ አወጣለሁ፥ አገርህንም አሰፋለሁ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም። |
በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
እስራኤልም ከሴቄም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም መፍራት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእስራኤልንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለአባቱ ለዳዊት በዘመኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎሞን በአባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገልጋዮቹን ወደ ሰሎሞን ላከ።
ያግቤጽም፥ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ ሀገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ምልክት አድርግልኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ የምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድንጋጤ ሆነ፤ ከኢዮሳፍጥም ጋር አልተዋጉም።
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
መልአኬንም ከአንተ ጋር በፊትህ እልካለሁ፤ ከነዓናዊውን፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውን፥ ኤዌዎናውዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ያወጣቸዋል።
በዚህ ቀን የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞሬዎናዊውን፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ከፊትህ አወጣለሁ።
“አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ ድንበርህን ባሰፋልህ ጊዜ፥ ሰውነትህም ሥጋ መብላት ስለ ወደደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ ሰውነትህ ከወደደችው ሁሉ ብላ።
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤
አምላክህም እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ዳርቻህን ቢያሰፋ፥ ለአባቶችህ እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረውን ምድር ሁሉ ቢሰጥህ፥
“አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከፊትህም ብዙና ታላላቅ አሕዛብን፥ ከአንተ የበለጡትን፥ የበረቱትንም ሰባቱን አሕዛብ፥ ኬጤዎናዊውን፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ባወጣ ጊዜ፥