በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
ዘፀአት 34:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጀመሪያ የሚወለድ ተባት ሁሉ የእኔ ነው፤ የላምህም በኵር፥ የበግህም በኵር፥ የበሬህም በኵር ሁሉ የእኔ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የመንጋህ ወይም የበግና የፍየልህ፣ የቀንድ ከብትህ ተባዕት በኵር ሁሉ ሳይቀር፣ ከማሕፀን በኵር ሆኖ የሚወጣ ሁሉ የእኔ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኅፀንን የሚከፍት ሁሉ የእኔ ነው፤ የከብትህም ተባዕት ሁሉ፥ የበሬህም፥ የበግህም በኩር የእኔ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በኲር ሆኖ የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ የእኔ ነው፤ የማንኛውም እንስሳ ተባዕት ሁሉ በሬም ሆነ በግ የእኔ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅፀንንም የሚከፍት ሁሉ የእኔ ነው፤ የከብትህም ተባት በኵር ሁሉ፥ በሬም ቢሆን በግም ቢሆን፥ የእኔ ነው። |
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለይ፤ ከመንጋህና ከከብትህም መጀመሪያ የሚወለደው ተባት ለእግዚአብሔር ይሆናል።
“በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም፥ ከእንስሳም መጀመሪያ የተወለደውን ማሕፀንን የሚከፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይልኝ፤ የእኔ ነው።”
የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ፥ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የአዝመራችሁን ቀዳምያት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።