ሰባት ቀን መሠዊያውን ታነጻዋለህ፤ ትቀድሰውማለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል፤ መሠዊያውንም የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።
ዘፀአት 30:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም አሠራር የዚህን ዕጣን ዐይነት ለእናንተ አታድርጉ፤ በእናንተም ዘንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለራስህ በዚያ ዐይነት መንገድ ምንም ዐይነት ዕጣን አታብጅ። ለእግዚአብሔር የተቀደሰ መሆኑን ልብ በል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራኸውን ዓይነት ዕጣን ለራሳችሁ አታድርጉ፤ በእናንተ ዘንድ ለጌታ የተቀደሰ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት የምታደባልቁትን ዕጣን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ አድርጉት እንጂ ለራሳችሁ መጠቀሚያ አታድርጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ እርሱ የተሠራ ዕጣን ለእናንተ አታድርጉ፤ በእናንተ ዘንድም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። |
ሰባት ቀን መሠዊያውን ታነጻዋለህ፤ ትቀድሰውማለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል፤ መሠዊያውንም የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።