La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 29:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዕለት ዕለ​ትም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረይ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም ባደ​ረ​ግህ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ቅዱ​ስም ይሆን ዘንድ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለማስተስረያ የሚሆን አንድ ወይፈን የኀጢአት መሥዋዕት አድርገህ በየዕለቱ ሠዋ፤ ለመሠዊያውም ማስተስረያ በማቅረብ መሠዊያውን አንጻው፤ ትቀድሰውም ዘንድ ቅባው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለማስተስረያ የሚሆን የኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን በየቀኑ ታቀርባለህ፤ በእርሱ ላይ ማስተስረያ በምታደርግበት ጊዜ መሠዊያውንም ታስተሰርይለታልህ፤ ቅዱስም እንዲሆን ትቀባዋለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለ ኃጢአትም ይቅርታ በእያንዳንዱ ቀን አንድ ኰርማ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤ ይህም መሠዊያውን ያነጻል፤ የተቀደሰም ይሆን ዘንድ የወይራ ዘይት ቀባው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዕለት ዕለትም ስለ ማስተስረይ ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈኑን ታቀርባለህ፤ ማስተስረያም ባደረግህ ጊዜ መሠዊያውን ታነጻዋለህ፤ ቅዱስም ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 29:36
14 Referencias Cruzadas  

የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት፥


ከደ​ሙም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በአ​ራቱ የመ​ሠ​ዊያ ቀን​ዶ​ቹም፥ በእ​ር​ከ​ኑም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም በአ​ለው ክፈፍ ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲሁ ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ታስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ት​ማ​ለህ።


ሰባት ቀንም በየ​ዕ​ለቱ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ከበ​ጎ​ችም አንድ ጠቦት በግ ያቀ​ር​ባሉ።


ቀኖ​ቹ​ንም በፈ​ጸሙ ጊዜ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ከዚ​ያም በኋላ ካህ​ናቱ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያደ​ር​ጋሉ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥


ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።