ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ አጥንቱንም ከእርሱ አትስበሩ፤ ከእርሱም እስከ ጥዋት የተረፈ ቢኖር በእሳት አቃጥሉት።
ዘፀአት 29:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቅድስናው መሥዋዕት ሥጋ ወይም እንጀራ እስከ ነገ ቢተርፍ፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የተቀደሰ ነውና አይበላም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከክህነቱ የአውራ በግ ሥጋ ወይም ከቂጣው እስከ ንጋት ድረስ ቢተርፍ አቃጥለው፤ የተቀደሰ ስለ ሆነ መበላት የለበትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተቀደሰው ሥጋ ወይም ቂጣ ተርፎ ቢያድር፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የተቀደሰ ስለሆነ አይበላም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሥጋውም ሆነ ከኅብስቱ ሳይበላ ተርፎ ያደረ ቢኖር በእሳት ይቃጠል፤ የተቀደሰ ስለ ሆነም መበላት የለበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተካኑበትም ሥጋ ወይም እንጀራ ተርፎ ቢያድር፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የተቀደሰ ነውና አይበላም። |
ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ አጥንቱንም ከእርሱ አትስበሩ፤ ከእርሱም እስከ ጥዋት የተረፈ ቢኖር በእሳት አቃጥሉት።
የበጉንም ስብ፥ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ላይ ያለውን ስብ፥ የቀኙንም ወርች ትወስዳለህ፤ የሚቀደሱበት ነውና።
“ለአሮንም ክህነት የታረደውን የአውራውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚለይ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትለየዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል።
ይህም የተለየ ቍርባን ነውና ከእስራኤልልጆች ዘንድ ለዘለዓለም የአሮንና የልጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የደኅንነት መሥዋዕታቸው የተለየ ቍርባን ይሆናል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን ይሆናል።
ሙሴም የኀጢአቱን መሥዋዕት ፍየል እጅግ ፈለገው፤ በፈለገውም ጊዜ እነሆ ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀሩትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቈጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፦