ዘፀአት 29:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የቅድስናውንም በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የክህነቱን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለክህነት ሥርዓት የቀረበውን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮንና ልጆቹ የክህነት ሥልጣን በሚቀበሉበት ጊዜ የታረደውን የአውራ በግ ሥጋ ወስደህ በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚካንበትንም አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ። |
እንዲህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ካህናቱ ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር፥ የእህሉን ቍርባን፥ የኀጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ።
ሙሴም ለቅድስና የሚሆነውን ሁለተኛውን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፤
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አላቸው፥ “ሥጋውን በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በተቀደሰው ቦታ ቀቅሉ፤ አሮንና ልጆቹ ይብሉት ብሎ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ በዚያ እርሱንና በቅድስናው መሶብ ያለውን እንጀራ ብሉ።
መሥዋዕት በሚሠዉ በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የነበረ የካህኑንም ሕግ አያውቁም ነበረ፤ ሕዝቡም ሁሉ መሥዋዕት በሠዉ ጊዜ የካህኑ ብላቴና ይመጣ ነበር፤ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበር፤
ደግሞም ስቡ ሳይጤስ የካህኑ ልጅ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።