ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተለየውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።
ዘፀአት 29:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአሮንም ክህነት የታረደውን የአውራውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚለይ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትለየዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአሮን ክህነት የአውራ በጉን ፍርምባ ከወሰድህ በኋላ እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዘው፤ ይህም የአንተ ድርሻ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሮን የክህነት ሥርዓት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ድርሻ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለአሮን ክህነት ሥርዓት ከታረደው የበግ አውራ ፍርምባውን ወስደህ ለእኔ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ መባ አድርገህ አንሣ፤ ይህም ለእናንተው የሚመደብ ድርሻ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንም ክህነት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል። |
ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተለየውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።
ካህኑም አንዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይለየዋል።
የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቍርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባውን በእግዚአብሔር ፊት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብና የፍርምባውን ስብ ያመጣል።
ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ።”
ሙሴም ከቅድስናው አውራ በግ ፍርምባውን ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበው ዘንድ ቈራረጠ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ይህ ለቅድስና ከታረደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።