የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታስቀምጣለህ።
ዘፀአት 29:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበጉንም ስብ፥ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ላይ ያለውን ስብ፥ የቀኙንም ወርች ትወስዳለህ፤ የሚቀደሱበት ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚህ አውራ በግ ሥቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃው ውስጥ ያለውን ስብ፣ የጕበቱን ሽፋን፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በዙሪያቸው ያለውን ሥብና ቀኙን ወርች ውሰድ፤ ይህ የክህነት አውራ በግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለክህነት ሥርዓት የቀረበ አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶቹ፥ በላያቸውም ያለውን ስብና የቀኙን ወርች ትወስዳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሚካኑበት ስለ ሆነ የአውራውን በግ ሞራ ላቱን፥ የውስጥ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ሞራ የተሻለውን ክፍል፥ ሁለቱን ኲላሊቶቹን፥ እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራና በቀኝ በኩል ያለውን የኋላ እግር ቈርጠህ ለያቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም የሚካኑበት አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች በላያቸውም ያለውን ስብ፥ የቀኙንም ወርች ትወስዳለህ። |
የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታስቀምጣለህ።
በመሠዊያውም ላይ ካለው ደም ከቅብዐት ዘይትም ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ ከእርሱም ጋር ባሉት በልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ትረጨዋለህ፤ እርሱም ልብሶቹም፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹ፥ ልብሶቻቸውም ይቀደሳሉ።
እነዚህም ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕቶች ለአንተና ለልጆችህ ሥርዐት እንዲሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመሥዋዕቱን ፍርምባና ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋርም ልጆችህ፥ ቤተሰብህም ተለይቶ በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ።
ካህኑም አንዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይለየዋል።
ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን፥ የኀጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።
የበሬውንና የአውራውንም በግ ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ ሁለቱን ኵላሊቶቹንም፥ በላያቸውም ያለውን ስብ፥ የጉበቱንም መረብ አመጡለት።
ወጥቤቱም ወርቹን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ሳሙኤልም፥ “ሳኦልን ለምስክር ከባልንጀራህ ተለይቶ ቀርቦልሃልና እነሆ፥ በልተህ የተረፈህን በፊትህ አኑር” አለው። በዚያም ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።