አውራውንም በግ ታርደዋለህ፤ ደሙንም ትወስዳለህ፤ የአሮንንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የቀኝ እጁንና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ጫፍ፥ የልጆቹንም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ታስነካለህ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ትረጨዋለህ።
ዘፀአት 29:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁለተኛውንም አውራ በግ ትወስደዋለህ፤ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ይጭናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌላውን አውራ በግ ወስደህ አሮንና ወንዶች ልጆቹ በራሱ ላይ እጆቻቸውን ይጭኑበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለተኛውን አውራ በግ ትወስደዋለህ፥ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ይጭናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለክህነት ሥርዓት የተመደበውን ሌላውንም አውራ በግ ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጃቸውን በራሱ ላይ እንዲጭኑበት ንገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛውንም አውራ በግ ትወስደዋለህ፤ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ይጭናሉ። |
አውራውንም በግ ታርደዋለህ፤ ደሙንም ትወስዳለህ፤ የአሮንንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የቀኝ እጁንና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ጫፍ፥ የልጆቹንም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ታስነካለህ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ትረጨዋለህ።
እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፤ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በሚቃጠለው መሥዋዕት፥ በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።