ዘፀአት 29:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውራውንም በግ በየብልቱ ትቈርጠዋለህ፤ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ ታጥባለህ፤ ከብልቱና ከራሱም ጋር ታኖረዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አውራ በጉን በየብልቱ ቈራርጠህ፣ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ዐጥበህ ከራሱና ከሌሎቹ ቍርጥራጭ ብልቶች ጋራ አኑረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውራውን በግ በየብልቱ ትቆርጠዋለህ፥ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ታጥባለህ፥ ከብልቱና ከራሱም ጋር ታኖረዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋውን በየብልቱ ቈራርጠው፤ የውስጥ ዕቃውንና የኋላ እግሮቹን በውሃ አጥበህ ከራሱና ከሌሎቹ የሥጋ ብልቶች ጋር አኑር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአውራውንም በግ በየብልቱ ትቆርጠዋለህ፥ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም ታጥባለህ፥ ከብልቱና ከራሱም ጋር ታኖረዋለህ። |
አውራንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥቡታል። ካህኑም ሁሉን በመሠዊያው ላይ ለቍርባን ያቀርበዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።