ዘፀአት 28:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀፍረተ ሥጋቸውንም ይከድኑበት ዘንድ የተልባ እግር ሱሪ ታደርግላቸዋለህ፤ ከወገባቸውም እስከ ጭናቸው ይደርሳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከወገብ ጀምሮ እስከ ጭን የሚደርስ ሰውነትን የሚሸፍን ከበፍታ የተሠራ የውስጥ ቍምጣ አብጅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀፍረተ ሥጋቸውን እንዲሸፍኑበት ከወገባቸው እስከ ጭናቸው የሚደርስ የበፍታ ሱሪ ታደርግላቸዋለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የውስጥ ሰውነታቸው እንዳይጋለጥ ከጥሩ በፍታ፥ ከወገባቸው እስከ ጭናቸው የሚደርስ ቊምጣ ሱሪ ትሠራላቸዋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኀፍረተ ሥጋቸውንም ይከድኑበት ዘንድ የበፍታ ሱሪ ታደርግላቸዋለህ፤ ከወገባቸውም እስከ ጭናቸው ይደርሳል፤ |
ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛውም አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ በአገለገሉ ጊዜ ከበግ ጠጕር አንዳች ነገር በላያቸው አይሁን።
በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፤ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚያልብ ነገር አይታጠቁ።
የተቀደሰውንም የተልባ እግር ቀሚስ ይልበስ፤ የተልባ እግርም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፤ የተልባ እግር መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የተልባ እግር አክሊልም በራሱ ላይ ያድርግ፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።
ካህኑም የተልባ እግር ቀሚስና የተልባ እግር ሱሪ በሰውነቱ ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።
ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ስለዚህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢአትን ለመሥራት ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ በሐሰት ቢምል፥
ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።