ለድንኳኑ ደጃፍም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ ከጥሩ በፍምታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አድርግለት።
ዘፀአት 28:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀሚሱንም ከጥሩ በፍታ ዝንጕርጕር አድርገህ፥ አክሊልን ከበፍታ ትሠራለህ፤ በጥልፍ አሠራርም መታጠቂያ ትሠራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሸሚዙን ከቀጭን በፍታ ሥራ፤ መጠምጠሚያውንም ከቀጭን በፍታ አብጀው፤ መታጠቂያውንም ጥልፍ ጠላፊ የሠራው ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጀ ጠባቡን ከጥሩ በፍታ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፥ በጥልፍ የተጠለፈ መታጠቂያ ትሠራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የአሮንን ሸሚዝና መጠምጠሚያ ከጥሩ በፍታ ሥራው፤ መታጠቂያውም ከጥሩ በፍታ ተሠርቶ በጥልፍ ጥበብ ያጌጠ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሸሚዙንም ከጥሩ በፍታ ዝንጕርጕር አድርገህ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፤ በጥልፍ አሠራር መታጠቂያም ትሠራለህ። |
ለድንኳኑ ደጃፍም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ ከጥሩ በፍምታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አድርግለት።
ለአደባባዩ ደጅም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከጥሩ በፍታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ ሃያ ክንድ መጋረጃ ይሆናል፤ ምሰሶዎቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ።
የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ ልብሰ እንግድዓ፥ ልብሰ መትከፍ፥ ቀሚስም፥ ዥንጕርጕር እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያ፥ መታጠቂያም፤ እነዚህንም በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን፥ ለልጆቹም የተቀደሰ ልብስ ያድርጉ።
ልብሶችን ወስደህ ለወንድምህ ለአሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መትከፍና ልብሰ እንግድዓ ታለብሰዋለህ፤ ለእርሱም ልብሰ እንግድዓውን ከልብሰ መትከፉ ጋር አያይዝለት።
የተቀደሰውንም የተልባ እግር ቀሚስ ይልበስ፤ የተልባ እግርም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፤ የተልባ እግር መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የተልባ እግር አክሊልም በራሱ ላይ ያድርግ፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።
ካህኑም የተልባ እግር ቀሚስና የተልባ እግር ሱሪ በሰውነቱ ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።