ልብሰ እንግድዓውም በብልሃት ከተጠለፈ ከልብሰ መትክፉ ቋድ በላይ እንዲሆን፥ ከልብሰ መትከፉም እንዳይለይ፥ ልብሰ እንግድዓውን ከቀለበቶቹ ወደ ልብሰ መትከፉ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል።
ዘፀአት 28:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰማያዊም ፈትል በመጠምጠሚያው ላይ በስተፊቱ ታንጠለጥለዋለህ ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመጠምጠሚያው ጋራ እንዲያያዝ ሰማያዊ ፈትል እሰርበት፤ እርሱም በመጠምጠሚያው ፊት በኩል ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ፈትል በመጠምጠሚያው ላይ ስፋው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጠምጠሚያውም ፊት በሰማያዊ ድሪ እንዲንጠለጠል አድርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰማያዊም ፈትል በመጠምጠሚያው ፊት ላይ ታንጠለጥለዋለህ። |
ልብሰ እንግድዓውም በብልሃት ከተጠለፈ ከልብሰ መትክፉ ቋድ በላይ እንዲሆን፥ ከልብሰ መትከፉም እንዳይለይ፥ ልብሰ እንግድዓውን ከቀለበቶቹ ወደ ልብሰ መትከፉ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል።
“ከጥሩ ወርቅም የወርቅ ቅጠል ሥራ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ፦ ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ትቀርጽበታለህ።
በአሮንም ግንባር ላይ ይሆናል፤ አሮንም የእስራኤል ልጆች በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱሱ ስጦታቸው ሁሉ ላይ የሠሩትን ኀጢአት ይሸከም፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀባይነት ያለው እንዲሆንላቸው ሁልጊዜ በግንባሩ ላይ ይሁን።
የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ ልብሰ እንግድዓ፥ ልብሰ መትከፍ፥ ቀሚስም፥ ዥንጕርጕር እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያ፥ መታጠቂያም፤ እነዚህንም በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን፥ ለልጆቹም የተቀደሰ ልብስ ያድርጉ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ አክሊል አደረገለት፤ በአክሊሉም ላይ በፊቱ በኩል የተቀደሰውን የወርቅ መርገፍ አደረገ።
ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፣ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እነርሱም በትውልዳቸው ሁሉ በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያደርጉ ዘንድ፥ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ እዘዛቸው።