ዘፀአት 28:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማገልገል ጊዜም በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በእግዚአብሔር ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም በአገልግሎቱ ጊዜ ይህን መልበስ አለበት፤ በእግዚአብሔር ፊት ወደ መቅደሱ በገባና ከመቅደሱ ሲወጣ እንዳይሞት የሻኵራዎቹ ድምፅ ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአገልግሎት ጊዜ በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በጌታ ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ ይህን ቀሚስ ይልበስ፤ በተቀደሰው ስፍራ በፊቴ በተገኘ ጊዜ ወይም ከዚያ በሚወጣበት ጊዜ የመርገፉ ድምፅ ስለሚሰማ ከመሞት ይድናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማገልገል ጊዜም በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በእግዚአብሔር ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል። |
“ከጥሩ ወርቅም የወርቅ ቅጠል ሥራ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ፦ ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ትቀርጽበታለህ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።