ዘፀአት 28:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሰ እንግድዓውም በብልሃት ከተጠለፈ ከልብሰ መትክፉ ቋድ በላይ እንዲሆን፥ ከልብሰ መትከፉም እንዳይለይ፥ ልብሰ እንግድዓውን ከቀለበቶቹ ወደ ልብሰ መትከፉ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደረት ኪሱም ቀለበቶች፣ የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋራ እንዳይላቀቅ፣ ከመታጠቂያው ጋራ በማገናኘት በሰማያዊ ገመድ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋራ ይያያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደረት ኪሱም በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረት ኪሱን ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደረት ኪሱ ላይ ያሉትን ቀለበቶች በኤፉዱ ላይ ካሉት ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ድሪ እሰራቸው፤ በዚህ ዐይነት የደረት ኪሱ ከመታጠቂያው በላይ ስለሚሆን ልል አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደረቱም ኪስ በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቍድ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረቱን ኪስ ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያስሩታል። |
ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፤ በልብሰ መትከፉ ፊት ከጫንቃዎች በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከልብሰ መትከፉ ቋድ በላይ በመጋጠሚያው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።
አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም መታሰቢያ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ ልብሰ እንግድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም።
በላዩም የተጠለፈው የልብሰ መትከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእርሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ፥ ከጥሩ በፍታም የተሠራ ይሁን።
በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች አመጡ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እነርሱም በትውልዳቸው ሁሉ በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያደርጉ ዘንድ፥ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ እዘዛቸው።