ከቤተ መቅደሱ አያይዞ ከመሠረቱ ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ ሃያውን ክንድ በዝግባ ጠርብ ሠራ፤ ከመቅደሱም ከፍሎ ቅድስተ ቅዱሳኑን አደረገ።
ዘፀአት 26:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጋረጃውንም በምሰሶዎች ላይ ስቀለው፤ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክሩን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጋረጃውን በማያያዣዎቹ ላይ ስቀለው፤ የምስክሩንም ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ አስቀምጠው፤ መጋረጃውም መቅደሱን ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጋረጃውንም ከመያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክርን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጋረጃውንም በድንኳኑ ጣራ ላይ በተርታ በተደረደሩት መያዣዎች ሥር ታንጠለጥለዋለህ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች የያዘውንም የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ በኩል ታኖረዋለህ፤ በዚህ ዐይነት መጋረጃው ቅድስት የተባለውን ስፍራ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጋረጃውንም ከመያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክርን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ። |
ከቤተ መቅደሱ አያይዞ ከመሠረቱ ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ ሃያውን ክንድ በዝግባ ጠርብ ሠራ፤ ከመቅደሱም ከፍሎ ቅድስተ ቅዱሳኑን አደረገ።
ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች ወደ ነበረው ወደ ስፍራዋ አገቧት።
ቅድስተ ቅዱሳኑንም ሠራ፤ ርዝመቱም እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ ስድስት መቶ መክሊት በሚያህል በጥሩ ወርቅም ኪሩቤልን ለበጣቸው።
በወርቅ በተለበጡት፥ ከማይነቅዝ ዕንጨትም በተሠሩት በአራቱ ምሰሶዎች ላይ ስቀለው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ፥ አራቱም እግሮቻቸው ከብር የተሠሩ ይሁኑ።
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
ከማይነቅዝም ዕንጨት አራት ምሰሶዎች አደረጉለት፤በወርቅም ለበጡአቸው፤ ኵላቦቻቸውም የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች አደረጉ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።