ዘፀአት 25:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሎጊያዎቹንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሥራ፤ በንጹሕ ወርቅም ለብጣቸው፤ ገበታውም በእነርሱ ይነሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሥራቸው፤ በወርቅ ለብጣቸው፤ ጠረጴዛውንም ተሸከምባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገበታውን እንዲሸከሙባቸው መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገበታውን ይሸከሙባቸው ዘንድ መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። |
ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭቶችዋን፥ ጭልፋዎችዋንም፥ መቅጃዎችዋንም፥ ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ተነሥና ሂድ፤ በአሕዛብና በነገሥታት፥ በእስራኤል ልጆችም ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና።