ዘፀአት 23:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔን እንድትበድል እንዳያደርጉህ በሀገርህ ላይ አይቀመጡ፤ አማልክቶቻቸውንም ብታመልክ ወጥመድ ይሆኑብሃልና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድርህ ላይ እንዲኖሩ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ እኔን እንድትበድል ያደርጉሃል፤ አማልክታቸውን ማምለክ በርግጥ ወጥመድ ይሆንብሃልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርህ አይቀመጡ አማልክቶቻቸውን በማገልገል እኔን እንድትበድል ያደርጉሃልና፥ ይህም ለአንተ ወጥመድ ይሆንብሃል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ሕዝቦች በአገርህ እንዲኖሩ አትፍቀድላቸው፤ የምትፈቅድላቸው ከሆነ ግን ኃጢአት በመሥራት እኔን እንድትበድል ያደርጉሃል፤ ለአማልክቶቻቸውም ብትሰግድ ለሞት የሚያደርስ ወጥመድ ይሆንብሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አማልክቶቻቸውንም ብታመልክ ወጥመድ ይሆኑብሃልና እኔን እንድትበድል እንዳያደርጉህ በአገርህ አይቀመጡ። |
ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።
የፈርዖንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እንቅፋት ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያመልኩት ዘንድ ሰዎችን ልቀቅ፤ ግብፅስ እንደ ጠፋች ገና አታውቅምን?” አሉት።
ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፤ ምስሎቻቸውንም ሰባብራቸው።
በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤
አምላኮቻቸውንም እንዳትሻ፥ አሕዛብም ለአምላኮቻቸው እንደሚያደርጉ እኔም አደርጋለሁ እንዳትል ራስህን ጠብቅ።
ለአማልክቶቻቸው ያደረጉትን ርኵሰት ሁሉ ታደርጉ ዘንድ እንዳያስተምሩአችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት እንዳትሠሩ ትረግማቸዋለህ።
“አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከፊትህም ብዙና ታላላቅ አሕዛብን፥ ከአንተ የበለጡትን፥ የበረቱትንም ሰባቱን አሕዛብ፥ ኬጤዎናዊውን፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ባወጣ ጊዜ፥
አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የአሕዛብ ምርኮ ትበላለህ፤ ዐይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ለአንተ ክፉ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ፥ ተራራማውን ሀገር፥ ደቡቡንም፥ ቆላውንም፥ ቍልቍለቱንም፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ መውደቂያና ወጥመድ፥ በእግራችሁም ችንካር፥ በዐይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንዳያጠፋቸው ራሳችሁ ዕወቁ።
እናንተም በዚች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አታድርጉ፤ ለአማልክቶቻቸውም አትስገዱላቸው፤ ምስሎቻቸውንም ስበሩ፤ መሠዊያቸውንም አፍርሱ አልሁ። እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም፤ ይህንስ ለምን አደረጋችሁ?
ስለዚህም እኔ አሕዛብን ከፊታችሁ አላወጣቸውም፤ ነገር ግን ያስጨንቋችኋል፤ አማልክቶቻቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል” አልሁ።
ሳኦልም፥ “እርስዋን እሰጠዋለሁ፤ እርስዋም እንቅፋት ትሆንበታለች” አለ። እነሆም፥ የፍልስጥኤማውያን እጅ በሳኦል ላይ ነበረች።