ዘፀአት 21:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰውም ጕድጓድ ቢከፍት ወይም ጕድጓድ ቢቈፍር ባይከድነውም፥ በሬም ወይም አህያ፤ ቢወድቅበት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ጕድጓድን ከፍቶ ቢተው፣ ወይም ጕድጓድ ቈፍሮ ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ጉድጓድ ቢከፍት፥ ወይም ጉድጓድ ቢቆፍር ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ቢወድቅበት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው የጒድጓድ መክደኛ ቢያነሣ ወይም ጒድጓድ ቆፍሮ ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ወደዚያ ጒድጓድ ቢገባ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ጕድጓድ ቢከፍት፥ ወይም ጕድጓድ ቢቆፍር ባይከድነውም፥ በሬም ወይም አህያ ቢወድቅበት፥ |
ለሰውነቴ ጕድጓድን ቈፍረዋል፤ በውኑ በመልካም ፈንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ፥ ቍጣህንም ከእነርሱ ትመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።
ሊይዙኝ ጕድጓድ ቈፍረዋልና፥ ለእግሮችም ወጥመድ ሸሽገዋልና፥ በቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድንገትም በላያቸው ወንበዴን አምጣባቸው።