በዚያች ሌሊትም አቤሜሌክ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር በሕልም ወደ እርሱ መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርስዋ ባለ ባል ናትና።”
ዘፀአት 12:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግብፃውያንም ፈጥነው ከምድሩ ይወጡ ዘንድ ሕዝቡን ያስቸኩሉአቸው ነበር፥ “ሁላችንም እንሞታለን” ብለዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብጻውያን አገራቸውን በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡላቸው እስራኤላውያንን አጣደፏቸው። “አለዚያማ ሁላችንም ማለቃችን ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግብፃውያንም ፈጥነው ከምድሩ እንዲወጡ ሕዝቡን ያስቸኩሉአቸው ነበር፥ “ሁላችንም ልንሞት ነው” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገሪቱን ለቀውላቸው እንዲወጡ ግብጻውያን ራሳቸውም ሕዝቡን በማጣደፍ “በአስቸኳይ ለቃችሁ ካልወጣችሁልን እነሆ ሁላችንም ማለቃችን ነው” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግብፃውያንም ፈጥነው ከምድሩ ይወጡ ዘንድ ሕዝቡን ያስቸኵሉአቸው ነበር፤ “ሁላችን እንሞታለን” ብለዋልና። |
በዚያች ሌሊትም አቤሜሌክ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር በሕልም ወደ እርሱ መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርስዋ ባለ ባል ናትና።”
ንጹሕ ደምንም አፈሰሱ፥ የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፥ ለከነዓን ጣዖቶች ሠዉ፥ ምድርም በደም ታለለች።
የፈርዖንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እንቅፋት ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያመልኩት ዘንድ ሰዎችን ልቀቅ፤ ግብፅስ እንደ ጠፋች ገና አታውቅምን?” አሉት።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ ገና አንዲት መቅሠፍት አመጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚያ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ከመነሻ ገንዘብ ጋር ይሰድዳችኋል።
ከግብፅም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ቂጣ እንጎቻ አድርገው ጋገሩት። አልቦካም ነበርና፤ ግብፃውያንም ስለ አስወጡአቸው ይቈዩ ዘንድ አልተቻላቸውምና፤ ለመንገድም ስንቅ አላሰናዱም ነበርና።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋልና፥ በተዘረጋችም ክንድ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ።”
እግዚአብሔር በፊታችሁ ይሄዳልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይሰበስባችኋልና በችኮላ አትወጡም፤ በመኮብለልም አትሄዱም።