የመንግሥቱ አለቆች ሁሉ ሹሞችና መሳፍንት፥ አማካሪዎችና አዛዦች፦ ንጉሥ ሆይ! ከአንተ በቀር ማንም እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ልመና ከአምላክ ወይም ከሰው ቢለምን፥ በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ይጣል የሚል የንጉሥ ሕግና ብርቱ ትእዛዝ ይወጣ ዘንድ ተማከሩ።