በመንግሥቴ ግዛት ሁሉ ያሉ ሰዎች በዳንኤል አምላክ ፊት እንዲፈሩና እንዲንቀጠቀጡ አዝዣለሁ፤ እርሱ ሕያው አምላክ ለዘለዓለም የሚኖር ነውና፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፥ ግዛቱም ለዘለዓለም ይኖራል።