ንጉሡም ዳንኤልን የከሰሱ እነዚያን ሰዎች ያመጡአቸው ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱንና ልጆቻቸውንም፥ ሚስቶቻቸውንም በአንበሶች ጕድጓድ ጣሉአቸው፤ ወደ ጕድጓዱም መጨረሻ ሳይደርሱ አንበሶች ያዙአቸው፤ አጥንታቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።