ወደ ጕድጓዱም በቀረበ ጊዜ በታላቅ ቃል ጮኸ፤ ንጉሡም ዳንኤልን፥ “የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ! ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች አፍ ያድንህ ዘንድ ችሎአልን?” አለው።